የሀገር ውስጥ ዜና

200 ቶን የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 13 ተሽከርካሪዎች መቀሌ ደረሱ

By Melaku Gedif

December 01, 2022

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 200 ቶን የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 13 ተሽከርካሪዎች በዛሬው ዕለት መቀሌ መድረሳቸውን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

መቀሌ ከደረሰው የሰብዓዊ እርዳታ መካከል ምግብ፣ መድሃኒት እና ለኩላሊት እጥበት የሚያገለግሉ የህክምና ሳሪያዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

እርዳታው ከኢትዮጵያ ስኳር ህመምተኞች ማህበር የተገኘ መሆኑን ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!