የሀገር ውስጥ ዜና

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

By Feven Bishaw

December 06, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር 2015 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም ከኅዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር 2015 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ  እንዲቀጥል የተወሰነ መሆኑን ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።