የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 14 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Mikias Ayele

December 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 14 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች መካከል 924ቱ ወንዶች፣ 63ቱ ሴቶች እንዲሁም 27  ተመላሾች ህፃናትና እድሜያቸው ከ18 አመት በታቸ የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ 12 ሺህ 857 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡