የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል እየመጣ ያለው ሰላም ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ ይመልስልናል – የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች

By Shambel Mihret

December 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል እየመጣ ያለው ሰላም ከቱሪዝም ያገኙት የነበረውን ገቢ እንደሚመልስላቸው በትግራይ ክልል የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

በክልሉ የነበረው ጦርነት ከቱሪዝም ያገኙት የነበረውን ገቢ በማቋረጡ በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረባቸው የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በአክሱም ከተማ ቅርሶችን በማስጎብኘት የሚተዳደሩ ግለሰቦች እንደሚሉት፥ በጦርነቱ ምክንያት ስራው በመቆሙ ከእነቤተሰቦቻቸው ለችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ።

አሁን እየመጣ ባለው ሰላም ግን የቱሪዝም ስራቸው ተመልሶ የኑሮ ሁኔታቸው እንደሚስተካከል ተስፋ እንዳላቸው ነው የሚናገሩት።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በከተማዋ እና በአካባቢው ባደረገው ቅኝት የአካባቢው ሰላም እየተመለሰ መሆኑን ተመልክቷል ።

በለይኩን ዓለም እና አፈወርቅ እያዩ