አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በጦርነቱ የወደሙ ተቋማት መልሶ ግንባታ መርሐ-ግብር ተጀመረ፡፡
የአማራ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ጦርነት አውዳሚና አጥፊ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ የገባችው ኅልውናን ለማስከበር እንጂ ፈቅዳ አይደለም ብለዋል።
“ተገደን በገባንበት ጦርነት በርካታ ወገኖችን አጥተናል፣ ከፍተኛ ሐብትና ንብረትም ወድሟል ሲሉ ነው የገለጹት።
ርዕሰ መስተዳድሩ በአንድነት ከቆምንና ከተባበርን የወደሙ መሠረተ-ልማቶችን በአጭር ጊዜ ከነበረው በተሻለ መልሰን እንገነባዋለንም ነው ያሉት።
በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች በጦርነት የወደሙ ተቋማትንና መሠረት ልማቶችን መልሶ መገንባትና ለማቋቋም አስፈላጊውን ሁሉ ርብርብ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።