አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፋግታ ለኮማ ወረዳ እንደውሃ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው ዛሬ ጠዋቱ 1 ሠዓት አካባቢ የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከባጃጅ ጋር ተጋጭቶ የተፈጠረ መሆኑን የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፓሊስ ጽኅፈት ቤት ባለሙያ ምክትል ኢኒስፔክተር አጥናፍ ፈረደ ገልጸዋል፡፡
በወቅቱ ሚኒባሱ ከአዲስ ቅዳም ወደ እንጅባራ በማምራት ላይ እንደነበረና ከእንጂባራ ወደ ኮሶበር ከሚሄድ ባጃጅ ጋር ተጋጭቶ አደጋው መከሰቱንም ጠቁመዋል፡፡
በዚህም ባጃጁ ውስጥ የተሳፈሩት ሦስት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ÷ በሌሎቹ ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡