የሀገር ውስጥ ዜና

የማሌ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ዶኦማ” እየተከበረ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

January 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማሌ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ዶኦማ” በሌሞ ጌንቶ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

የማሌ ብሔረሰብ በደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙት 16 ብሔር ብሔረሰቦች አንዱ ሲሆን÷ በየዓመቱ ጥር 1 ወይም በብሔረሰቡ አጠራር “ባሬ ፔተ” አዲሱን ዓመት ይቀበላሉ።

“ዶኦማ”÷ ማብሰር፣ መጀመር፣ መቅመስ፣ መክፈት፣ ቅድሚያ የሚሉ ፍቺዎች እንዳሉት ከጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአከባበር ሥነ ስርዓቱ ላይ÷ የፌደራል፣ የክልል፣ የአጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች፣ የጋሞ ዞን አመራሮች፣ የጋሞ አባቶች እንዲሁም ከሰሜን ኬንያ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ቦርጂ፣ ኮንሶ፣ ባስኬቶ እና ሌሎች አካባቢዎች የመጡ እንግዶች በሌሞ ጌንቶ ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!