የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደሮች በጎንደር ከተማ የፋሲል ግንብን ጎበኙ

By Melaku Gedif

January 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን የሚወክሉ አምባሳደሮች በጎንደር ከተማ ታሪካዊና ጥንታዊውን የፋሲል ግንብ ጎብኝተዋል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተሳትፈዋል።

አምባሳደሮቹ በቀጣይ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የተለያዩ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራዎች እንዲጎበኙ የማድረግ ስራ እንዲሚያከናውኑ ይጠበቃል።

ለዚህም ያደረጉት ጉብኝት የበለጠ አቅም እንደሚፈጥርላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በሀብታሙ ተ/ስላሴ