የሀገር ውስጥ ዜና

ባንኩ በሞባይል ባንኪንግ የዓየር መንገድ ትኬት የሚገዙ ደንበኞቹ ላይ የጣለውን የብር ገደብ አነሳ

By Alemayehu Geremew

January 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሞባይል ባንኪንግ የዓየር መንገድ ትኬት ለመግዛት ከዚህ በፊት የነበረውን የ100 ሺህ ብር ገደብ ማንሳቱን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ደንበኞቹ የበረራ ትኬት ለመግዛት የብር ኖት መያዝ ሳያስፈልጋቸው በሞባይል ባንኪንግ ያለገደብ ግዢ መፈጸም እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡