የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም ሶስት የተለያዩ የደንበኞች አገልግሎቶችን አስጀመረ

By Tamrat Bishaw

January 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የክላውድ፣የሙዚቃ ስትሪሚንግ እና የቴሌ ድራይቭ የሞባይል መረጃ ቋት አገልግሎቶችን ከአጋሮች ጋር ስምምነት በመፈፀም በይፋ አስጀምሯል።

ተቋሙ ቴሌ ድራይቭ፣ እልፍ ፕላስ እና ክላውድ ሶልሽን የተሰኙ ሶስት የተለያዩ መተግበሪያዎችን ነው ይፋ ያደረገው።

በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ቴሌድራይቭ የለያዩ ፋይሎችን ለመጠባበቂያነትና ለማስቀመጥ የሚረዳ መሆኑ ተብራርቷል።

እልፍ ፕላስ የተሰኘው መተግበሪያ ደግሞ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ኦንላይን ለማድመጥና ለማውረድ የሚያገለግል መተገበሪያ መሆኑ ነው የተመላከተው፡፡

ክላውድ ሶልሽን የተሰኘው መተግበሪያ በተለያዩ መንገዶች የተዘጋጁ የግልም ሆነ የተቋማት መረጃዎችን ለመሰነድ ያገለግላል ተብሏል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ