የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ሊያ ታደሰ ከአዲሱ የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

February 06, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከአዲሱ የዓለም አቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ አቡባካር ካምፖ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በትብብር በሚከያከናውኗቸው የህጻናት ጤና፣አልሚ ምግብ፣ ለአስቸኳይ ጊዜ በሚሰጥ ምላሽ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ ዩኒሴፍ ለኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ለሚያደርገው ድጋፍና የሚያሳውን አጋርነት አድንቀዋል።

በቀጣይም ከድርጅቱ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!