የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች ከኬሊማን ከተማ ከንቲባ ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

February 08, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሞዛምቢክ ውስጥ ከምትገኘው ኬሊማን ከተማ ከንቲባ ማኑኤል ዲ አራዦን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ግንኙነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ሁለቱን ከተሞች በኢንቨስትመንት፣ በኮንስትራክሽንና ሪልስቴት፣ በባህል ልውውጥ እንዲሁም የእህትማማችነትን ግንኙነት በሚያቀራርቡና በሚያጠናከሩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡