የሀገር ውስጥ ዜና

በደረሰ የእሳት አደጋ በ9 መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ

By Meseret Awoke

February 15, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በደረሰ የእሳት አደጋ በዘጠኝ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በእሳት አደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡

በኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ልዩ ቦታው 31 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከረፋዱ 4፡25 ላይ በመኖሪያ ቤቶች የደረሰው የእሳት አደጋ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

አደጋውን ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ተሰማርቷል፡፡

በንብረት ላይ የደረሰው የውድመት መጠንና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!