አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ተገቢውን ስራ አልሰራም በሚል በአሜሪካ መንግስት እና በሌሎች አካላት በድርጅቱ እና በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ላይ ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ ነው።
ይህንን ተከትሎም የአፍሪካ ህብረትና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በአሜሪካ መንግስት አና በሌሎች አካላት የሚፈጠሩ ጫናዎችን በመቃወም ድጋፋቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት እና ለድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።