የሀገር ውስጥ ዜና

36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ተጀምሯል

By Shambel Mihret

February 18, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

42ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሕብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ተወካዮች በተገኙበት መካሄዱ ይታወቃል፡፡

የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ በውይይቱ ያጸደቃቸውን አጀንዳዎች ለ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የሚያቀርብ ይሆናል።