ጤና

ከ60 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ እናት 8 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጢ ተወገደ

By Alemayehu Geremew

February 20, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ60 ዓመት የዕድሜ በለጸጋ እናት 8 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጢ ማስወገድ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በሆስፒታሉ ስኬታማ ነው የተባለለትን ቀዶ ጥገና ያደረጉት እና የቀዶ ጥገናውን ቡድን የመሩት የማህጸን እና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ጌታቸው የተባሉ ሐኪም መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ቀዶ ጥገናው 2 ሠዓት ከ 20 ደቂቃ እንደፈጀም ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው እናት ከቀዶ ጥገናው በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡