የሀገር ውስጥ ዜና

በባምባሲ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እየተሠራ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

February 21, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከምዕራብ ወለጋ ዞን እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ወረዳዎች በጸጥታ ችግር ተፈናቅለው በባምባሲ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የምዕራብ ወለጋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተሊላ ተረፈ÷ ከመነሲቡ፣ መንዲ፣ በጊ እና ቁንዳላ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ወገኖች ባምባሲ መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

በተሠራው የተቀናጀ ሥራም ከመነሲቡ እና መንዲ ወረዳዎች የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው መመለስ መቻሉን ነው የጠቆሙት።

ከበጊና ቁንዳላ ወረዳዎች የተፈናቀሉትን ለመመለስም ከወረዳዎቹ አስተባባሪ ኮሚቴ ተዋቅሮ ቅድመ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ተፈናቃዮቹን ወደቀያቸው እንዲመለሱ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ቤታቸው ስለወደመ በወረዳ ደረጃ እየተዘጋጀ ያለ መጠለያ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም አቅሙ ያላቸው ደግሞ ወደ ወረዳቸው ተመልሰው በኪራይ መኖር እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በንቲ አበሹ እደገለጹት÷ ከክልሉ ቶንጎ እና ሰዳል ወረዳዎች ተፈናቅለው በመጠለያው ያሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በቅንጅት እየተሠራ ነው፡፡

በመጠለያ ጣቢያው ለሚገኙ ወገኖች የክልሉ መንግሥት ምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑንም አንስተዋል።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!