አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከየካቲት 15 እስከ 19 ቀን 2015 ዓ.ም በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 1ኛው የኢትዮጵያ ኘሮጀክቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ተጠናቀቀ።
የኦሮሚያ ክልል ውድድሩን በማሸነፍ ዋንጫ ተሸልሟል፡፡
አማራ ክልል ሁለተኛ እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸውን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡