የሀገር ውስጥ ዜና

ከአሊ ባባ ግሩፕ ጋር በኢ-ኮሜርስ ግብይት በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

By Melaku Gedif

February 28, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በቻይና የአሊ ባባ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝታቸውም ከአሊ ባባ ግሩፕ ምክትል ፕሬዚዳንት ሊዩ ናን ጋር በቀጣይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡

በተለይም ከአሊ ባባ ግሩፕ ጋር በኢ-ኮሜርስ እና ዲጂታል ግብይት ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡