የሀገር ውስጥ ዜና

ስድስተኛው ዙር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና መጋቢት 4 ቀን ይጀመራል

By Melaku Gedif

March 07, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስድስተኛው ዙር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀመር የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ÷ በስልጠናው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ ከ15 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።

በጎ ፈቃደኞቹ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች በመሰማራት በተለያዩ ዘርፎች ነጻ አገልግሎት እንደሚሰጡ አመላክተዋል።

የበጎ ፈቃድ ስልጠናው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን÷ በስራ ፈጠራ፣ ስነ ልቦና እና ተጓዳኝ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።

ባህር ዳር፣ ጅማ፣ ዋቻሞ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠናው የሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡