የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ምክትል ከንቲባ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

March 08, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ምክትል ከንቲባ ሊ ቻንግ ዎ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት ውይይቱ ለ19 ዓመታት የዘለቀውን የአዲስ አበባ እና የቹንቾን ከተሞች ወዳጅነት በሚቀጥልበት፣ በልምድ ለውውጥ እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

የቹንቾን ከተማ ልዑካን ቡድን አባላት ለአብርሆት ቤተመፅሐፍት ላደረጉት ድጋፍ እና በኮሪያ ዘማች ኢትዮጵያውያን ሙዚየም ስላደረጉት ጉብኝት ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡