የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሎችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት አፈ-ጉባዔዎች ጋምቤላ ገቡ

By Meseret Awoke

March 14, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ጋምቤላ ከተማ ገብተዋል፡፡

አፈጉባኤዎቹ ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አፈ-ጉባኤዎቹ በጋምቤላ በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን የመስክ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!