አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዳዲስ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡
ሹመቶቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ በሚገኝበት ወቅት ነው፡፡ በዚህም ፡-
1. ዶክተር ጀማሉ ጀንበሩ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ ውበትና ልማት ቢሮ ሃላፊ
2. አቶ ቢኒያም ምክሩ – የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ
3. አቶ አብርሃም ታደሰ – የአዲስ አበባ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ
4. አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን – የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
5. አቶ አደም ኑሪ – የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ
6. አቶ በላይ ደጀን – የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
7. ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ – የአዲስ አበባ የቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ሃላፊ
8. አቶ ካሳሁን ጎንፋ – የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ
9. አቶ አያሌው መላኩ – የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና አቤቱታ ሰሚ ጉባዔ ሃላፊ
10. ወ/ሮ እናታለም መለሰ – የአዲስ አበባ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሹመታቸው በሙሉ ድምፅ ጸድቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተሿሚዎቹ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል ።
በመሳፍንት እያዩ
#Ethiopia #AddisAbaba
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!