አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነት እንደምታጠናክር ተናገሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነው።
በመግለጫቸውም÷ በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ላይ በሁለቱም ወገን የተጠናከረ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አንስተዋል።
ዘላቂ ሰላም ለማምጣትም የሽግግር ፍትህን አጠናክሮ መተግበር እና ሃገራዊ ምክክር ማከናወን ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!