አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ተመስገን ዘውዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
አቶ ተመስገን ባደረባቸው ህመም ሳቢያ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ህይዎታቸው አልፏል።
ከ1998 እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ ቅንጅት ለአንድነትን በመወከል የፓርላማ አባል በመሆን አገልግለዋል።
አቶ ተመስገን ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበሩ።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision