አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ከአውስትራሊያ ዶክተርስ ፎር አፍሪካ ተራድኦ ድርጅት ሊቀመንበር ግራህም ፎርዋርድ ጋር ተወያዩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይታቸው÷ በክልሉ የሚገኙና ድጋፍ የሚሹ የሕክምና ተቋማትን በተመለከተ ለሊቀመንበሩ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ለአካባቢ ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህ በፊት ለሆስፒታሉ የተደረገው ድጋፍ የክልሉን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይታመናል መለታቸውን ከርዕሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአውስትራሊያ ዶክተርስ ፎር አፍሪካ ተራድኦ ድርጅት ሊቀመንበር ግራህም ፎርዋርድ በበኩላቸው በክልሉ ለሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች ተቋማቸው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡