የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት የመንግስትን የስድስት ወር ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ

By Melaku Gedif

March 27, 2023

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት የመንግስትን የስድስት ወር አፈጻጸም ሪፖርት ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚያቀርቡት ሪፖርት ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

የስብሰባው አጠቃላይ ሂደትም ከዋናው አዳራሽ በቀጥታ ስርጭት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በምክር ቤቱ የፌስቡክ ገጽና በዩ ቲ ዩብ ቻናል እንደሚተላለፍ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።