አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጾም ወቅት የደም ለጋሾች ቁጥር ስለሚቀንስ በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
በተያዘው የጾም ወቅት በቂ ደም ከማግኘት አንፃር ውስነነት መኖሩን የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ሕይወትን ማትረፍ ከፆሙ ዓላማ አንፃር ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለሆነ ከአፍጥር እና ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ለመታደግ ሕብረተሰቡ በንቃት ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ደም የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ሕይወት ለመታደግ በተንቀሳቃሽ እና በቋሚ ቦታዎች ደም የማሰባሰብ ሥራው እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ሕብረተሰቡም የወገኑን ሕይወት ለመታደግ በንቃት ደም እንዲለግስ ጠይቀዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!