የሀገር ውስጥ ዜና

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮንትሮባንድ ንግድን በቅንጅት ለመቆጣጠር እየመከረ ነው

By Alemayehu Geremew

March 29, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮንትሮባንድ ንግድን በቅንጅት ለመቆጣጠር ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ በክልሉ የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ የኮንትሮ ባንድ ንግድ በዘላቂነት መከላከልና በተቀናጀ አግባብ መቆጣጠር የሚያስችል የጋራ አቅጣጫ እንደሚያዝ ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሐሰንን ጨምሮ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ ፣ የተለያዩ የክልልና የፌዴራል ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት መገኘታቸውን የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር ፅኅፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡