የሀገር ውስጥ ዜና

ጤና ሚኒስቴርና “ቡርጄል ሜዲካል ሲቲ” አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

By Alemayehu Geremew

March 30, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አቡዳቢ ከተማ የሥራ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው በቆይታቸው በአቡዳቢ ከሚገኘው “ቡርጄል ሜዲካል ሲቲ” የተሰኘ ግዙፍ ሁሉን ዓቀፍ የሕክምና ተቋም ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ከተቋሙ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውንም ዶክተር አየለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

“ቡርጄል ሜዲካል ሲቲ” ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ በሁሉም ዘርፍ የሕክምና አገልግሎት የሚሠጥ ግዙፍ የግል ተቋም ነው፡፡