የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

March 31, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፕሬዚዳንቱን በቢሯቸው ተቀብለው እንዳነጋገሩ አስፍረዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ፣ በክልላዊ እና በባለ ብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኮሞሮስ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ እና በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ለማጠናከርም እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት አዛሊ የመጡት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት የስራ ጉብኝት ለማድረግ መሆኑም ተገልጿል።