አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ከንቲባ አዳነች 150 አቅመ ደካሞች ፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች እንዲሁም 50 ለወንዝ ዳርቻ ልማት ተነሺዎች የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን አስረከቡ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷የምንሰራው ስራ ለአዲስ አበባ ነዋሪ ያለንን ሃብት በጋራ የምናካፍልበት ነው ብለዋል፡፡
ለከተማዋ ነዋሪ የቤት ጉዳይ አንገብጋቢ መሆኑን በመረዳት ችግሩን ለመፍታት ከግል ባለሀብቶች ጋር በመሆን አሁን ላይ ከ20 ሺህ በላይ ቤቶች መገንባት መቻሉን ገልፀዋል።
እየተሰራ ያለው ስራ ሰራን ብለን የምንኩራራበት ሳይሆን መስራት እንደምንችል ማሳያ ነው ያሉት ከንቲባዋ በልማት አማካኝነት የሚነሱ ዜጎችን ለመደገፍ ሌሎች ባለሀብቶችም ተባባሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።
በዛሬው ዕለት 50 የሚሆኑ የልማት ተነሺዎች ቤት የተረከቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በቀጣይ በሌሎች ክፍለ ከተሞች ይረከባሉ ተብሏል።
በዘመን በየነ