አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የተመራ ልዑክ በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ ላይ ያለውን የሆርቲካልቸር ክላቨር የአበባ ምርትን ጎበኘ፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በዚሁ ወቅት÷እንደ ሀገር ያለውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት ብዙ እንቅስቃሴ እየተደረገ በመሆኑ በትንሽ ቦታ ሰርቶ ብዙ ገቢ ማግኘት እንደምንችል ይህ ድርጅት ማሳያ ነው ብለዋል።
ተቋሙ ለብዙዎች የስራ ዕድል እንደፈጠረ እና በዓመት 400 ሚሊየን ዩሮ ገቢ ማስገኘት እንደቻለም ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡