አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከናወኑ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ።
የግብርና ሚኒስትሩ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሻድሊ ሀሰን እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ የተከናወኑ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ÷ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልምአርሶ አደሩን በማሳተፍ የተከናወኑ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራዎች የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በቀጣይ የክልሉን የስንዴ ልማት ሥራ ለማጠናከር አስፈላጊ ግብዓቶችን እንደሚያቀርብም ገልጸዋል።
አቶ አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው÷ የክልሉ መንግሥት ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ አመራሩን በማሰማራትድጋፍ እና ክትትል በመደረጉ አሁን ላይ የተሻለ ተሞክሮ የተያበት የስንዴ ልማት መከናወኑን ገልጸዋል።
በመስክ ጉብኝቱ የተገኙት በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሚስተር ኦስማኔ ዲዎን÷ በክልሉ በተመለከቱት የስንዴ ልማት ሥራ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ባንኩ የማሽነሪ እና የግብዓት አቅርቦት ላይ ትኩረት በመስጠት ለክልሉ የግብርና ዘርፍ ዕድገት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል ማለታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!