ስፓርት

አትሌት አበጀ አያና የፓሪስ ማራቶንን አሸነፈ

By ዮሐንስ ደርበው

April 02, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት አበጀ አያና ዛሬ የተካሄደውን የፓሪስ ማራቶን አሸነፈ፡፡

አትሌት አበጀ ውድድሩን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ነው።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጉዬ አዶላ 2 ሰዓት 7 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን መጨረሱን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

እንዲሁም ኬንያዊው አትሌት ጆስፋት ቦይት ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!