አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በአማራ ክልል የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር እታገኝ አደም ከተለያዩ ክልሎች ተፈናቅለው በክልሉ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ መድረሱን ገልጸዋል፡፡
ከፌደራል መንግስት በተጨማሪ በክልሉ በጀት ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ ቢሆንም÷ በየጊዜው የሚመጡ አዳዲስ ተፈናቃዮች በመኖራቸው መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡
ለዚህም ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሜሪጆይ ኢትዮጵያ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከዳያስፖራው ማሕበረሰብ እና ከአርቲስቶች ያሰባሰበውን ከ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ዛሬ አስረክቧል፡፡
ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሜሪጆይ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዘቢደር ዘውዴ ተናግረዋል፡፡
በኤልያስ ሹምዬ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!