የሀገር ውስጥ ዜና

የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

By Mikias Ayele

April 03, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራ የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦር አመራር መኮንኖች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡

ጄኔራል መኮንኖቹ  የኢንስቲትዩቱን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዓቅም እና እየተከናወኑ ያሉ የምርምር እና ልማት ስራዎችን  ተመልክተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ  ጋቸና÷ ኢንስቲትዩቱ እያከናወናቸው ባሉ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የጎሉ የምርምር እና ልማት ስራዎች ዙሪያ ለቡድኑ አባላት ገለጻ አድርገዋል፡፡

የኤርትራ የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦሩ አመራሮች ቡድን አስተባባሪ ጄኔራል አብርሃ ካሳ  በበኩላቸው÷ በኢንስቲትዩቱ ያደረጉት ጉብኝት ለሀገራቸው ብዙ ልምድ የቀሰሙበት መሆኑን ተናገረዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቴክኖሎጂው ዘርፍም አብረው መስራት የሚያስችላቸው እድል ስለመኖሩም የተገነዘቡበት ጉብኝት መሆኑን መግለፃቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡