አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ከአበርገሌ ወረዳ ተፈናቅለው በሰቆጣ ከተማ መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ከ37 ሺህ በላይ ወገኖች ወደ ቀያቸው መመለስ ጀመሩ፡፡
ተመላሾቹ በግጭቱ ምክንያት ከቀያቸው ከተፈናቀሉ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኗቸዋል ተብሏል፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እንደገለጹት÷ በዞኑ 67 ሺህ 961 ተፈናቃዮች ይገኛሉ፡፡
ከነዚህ መካከል ዛሬ በሰቆጣ ከተማ መጠለያ ጣቢያ የነበሩ 37 ሺህ የሚሆኑ የአበርገሌ ወረዳ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ ተጀምሯል ብለዋል፡፡
አሁን ላይ የአበርገሌ ወረዳ የፀጥታ ሁኔታ አንጻራዊ ሰላም የሚታይበት መሆኑን የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!