የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተወያዩ

By Melaku Gedif

April 04, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሀገራቱ የድንበር አዋሳኝና ከቀጠናው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አንፃር አብረው መስራት በሚገባቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረው መግባባት ላይ መድረሳቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡