አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅትን (ኔቶ) በይፋ ተቀላቅላለች፡፡
የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ሀገራቸው ኔቶን የተቀላቀለችበትን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አስረክበዋል።
ይህን ተከትሎም የፊንላንድ ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ ብራስልስ በሚገኘው የኔቶ ዋና መስሪያ ቤት ከፍ ብሎ ተውለብልቧል፡፡
በዚህም ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) 31ኛ አባል ሀገር መሆን መቻሏን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!