የሀገር ውስጥ ዜና

ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

By Amele Demsew

April 04, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ያላቸውን የሁለትዮሽ እና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ ÷ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ወሳኝ ሚና ያላት ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

የጣሊያን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛ እንደሆነ ማረጋገጣቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡