የሀገር ውስጥ ዜና

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በሶስት ሳምንታት ውስጥ 500 ሚሊየን ብር የቦንድ ግዢ መፈጸም የሚያስችል ንቅናቄ ሊያካሂድ ነው

By Amele Demsew

April 06, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 12ኛ አመትን ምክንያት በማድረግ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በሶስት ሳምንታት ውስጥ 500 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዢ መፈጸም የሚያስችል ንቅናቄ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል።

ንቅናቄው “ወጣት ለህዳሴው እኔም ድርሻ አለኝ” በሚል መሪ ሀሳብ መጋቢት 30 ቀን በድሬዳዋ ከተማ በይፋ የሚጀመር ሲሆን በሶስት ሳምንታት ውስጥ 500 ሚሊየን ብር የቦንድ ግዢም ለማካሄድ ያለመ ነው ተብሏል።

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፅፈት ቤት ሀላፊ አባንግ ከመዳን ከዚህ ቀደም ወጣቱ በተለያዩ ሀገራዊ ሁነቶች ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ ሲያበረክት እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በቦንድ ግዢ ንቅናቄው ላይ ሁሉም በመሣተፍ አሻራውን ማሣረፍ እንደሚገባውም ተናግረዋል፡፡

የቦንድ ግዢው አስተባባሪና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማሥተባበሪያ ፅፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሀይሉ አብረሀም በበኩላቸው÷ የግድቡ 12ኛ አመት በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር እንደቆየ አንስተው በሚያዚያ ወር በሚደረገው ንቅናቄ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን በድሬዳዋ ከተማ ጅማሮውን የሚያደርገው ንቅናቄው ማገባደጃውን በአሶሳ ከተማ ያደርጋልም ተብሏል።

በቤተልሄም መኳንንት

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!