የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በሕገ ወጥ የእህል ምርት አቅራቢዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

April 07, 2023

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በሕገ ወጥ የእህል ምርት አቅራቢዎች የሚደረጉ ግብይቶች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡

ከሕገ ወጥ አካላት ጋር የሚደረግ ማንኛውም ግብይት ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ቢሮው ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡

ቢሮው ከወፍጮ ባለንብረቶችና ከነጋዴ አደረጃጀቶች ጋር የኑሮ ውድነት ጫናን በዘላቂነት ለማርገብ ያለመ ውይይት አካሂዷል፡፡

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ እየደረሰ ያለውን የኑሮ ጫና በዘላቂነት ለማርገብ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚጠበቅበት መገለጹን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቂ የእህል ምርት ወደ ከተማዋ እየገባ በመሆኑ ምንም ዓይነት የምርት እጥረት በሀገር አቀፍ ደረጃ አለመኖሩን የገለጸው ቢሮው÷ ይህ ባልሆነበት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝቧል፡፡

ጤፍን ጨምሮ የእህል ግብይት ላይ ሕገ ወጦች በሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ምክንያት አላስፈላጊ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!