የሀገር ውስጥ ዜና

በግብርና ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ስራዎችን ጎበኘ

By Feven Bishaw

April 07, 2023

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በግብርናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎብኝቷል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

ልዑኩ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የሌማት ትሩፋት ስራዎች እንዲሁም በቡና እና ቅመማ ቅመም ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡

በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ አርሶ አደሮች በግብዓት እና በምርጥ ዘር አቅርቦት እና በሌሎች ችግሮች ላይ ጥያቄ አቅርበዋል።

በአርሶ አደሮች የተነሱ ጥያቄዎች በአፋጣኝ ምላሽ እንደሚያገኙም ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተዋል።

በፍሬው አለማየሁ