የሀገር ውስጥ ዜና

ተቋማት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጄክት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደቀጠሉ ነው

By Mikias Ayele

April 08, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቋማት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጄክት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደቀጠሉ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ4ኛ ዙር የገበታ ለትውልድ ፕሮጄክትን የደገፉ ድርጅቶችን በመዘርዘር አመስግኗል፡፡

በዚህም መሰረት ዳሸን ባንክ 72 ሚሊየን ብር፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 51 ሚሊየን ብር፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 25 ሚሊየን ብር እና የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ 16 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ሴንቹሪ ግሩፕ 20 ሚሊየን ብር፣ ፊሰን ሪል ስቴት 13 ሚሊየን ብር እንዲሁም ጊፍት ሪል ስቴት የ12 ሚሊየን ብር  ድጋፍ ያደረጉ ድርጅቶች ናቸው፡፡