የሀገር ውስጥ ዜና

የመደመር ትውልድ መጽሐፍ የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

April 08, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመደመር ትውልድመጽሐፍ የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ ክልላዊ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በጋምቤላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ÷በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በክልሉ ለቤተ መጸሐፍት ማሰሪያ እንደሚውል ገልፀዋል፡፡

የመደመር ትውልድ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና በማሸጋገር ትልቅነቷን እንደሚያረጋግጥ እምነት የሚጣልበት መሆኑንም  ጠቅሰዋል።

ሁሉም መጽሐፉን በመግዛት በትውልድ ግንባታ ሂደት የበኩላቸውን እንዲወጡ  ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ  ማቅረባቸውን ከጋምቤላ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡