የሀገር ውስጥ ዜና

ዛሬ ለሚካሄደው የጎዳና ላይ ኢፍጣር የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

By Mikias Ayele

April 08, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ለሚካሄደው የጎዳና ላይ ኢፍጣር የፅዳት ዘመቻ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል::

በፅዳት ዘመቻው ላይ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የታለቁ የረመዳን   ፆም የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዛሬ ምሽት ከ12 ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል፡፡