የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የተካሄደው የኢፍጣር ሥነ ስርዓት በሰላም ተጠናቋል- ፖሊስ

By ዮሐንስ ደርበው

April 08, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለሦስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢፍጣር ሥነ ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የከተማዋ ነዋሪ በተለይም የሙስሊሙ ማሕበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር  ማድረጉን የገለጸው ፖሊስ ለዚህ በጎ ተግባር ምስጋና አቅርቧል፡፡

እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላትም ፖሊስ አመስግኗል፡፡

የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር በሚሠሩ ልዩ ልዩ ተግባራት ሕብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!