የሀገር ውስጥ ዜና

ከሙስና ጥቆማ በኋላ ያለው ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራ ለሌላ ዙር ሌብነት የተጋለጠ መሆኑ ተመለከተ

By ዮሐንስ ደርበው

April 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች በብዛት እንደሚቀርቡ የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች የጋራ የትስስር ጉባዔ በአዳማ እየተካሄደ ነው፡፡

የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች በብዛት እንደሚቀርቡ ተናግረዋል፡፡

ከጥቆማ በኋላ ያለው የምርመራ እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራ ግን ለሌላ ዙር ሙስና ወይም ሌብነት የተጋለጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሕብረተሰቡ በሙስና ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ የሚያቀርበውን ጥቆማ በመጠቀም ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራዎች ችግር የበዛባቸው መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

የመረጃ ቸርቻሪዎች ወይም መረጃን የሚያሾልኩ ኃይሎች በጥቆማ የመጡ የሙስና ወንጀሎች ውጤታማ የምርመራ ሥራዎች እንዳይሠሩባቸው እያደረጉ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሙስናን የመከላከል ሥራ ሀገርን የማስቀጠል ጉዳይ እንደሆነ አንስተው÷ ሌብነት ፈፅመው በብሔር፣ በሃይማኖት እና በትውውቅ ለመደበቅ የሚሞክሩ አካላት ስለመኖራቸው አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!