አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት አባል ሀገራት (ኔቶ) ከፍተኛ የዓየር ኃይል ልምምድ ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በጀርመን ጦር ኃይሎች መሪነት ይካሄዳል የተባለው ይኼው ልምምድ 10 ሺህ ያኅል ወታደሮችንና 220 የጦር አውሮፕላኖችን ያሳትፋል ተብሏል፡፡
ልምምዱ በአውሮፓ የዓየር ክልል ላይ የሚካሄድ ሲሆን 100 ያኅል የጦር አውሮፕላኖችን አሜሪካ እንደምታዋጣ ተጠቁሟል፡፡
የጀርመን ጦር ኃይሎች በመግለጫው እንዳስታወቀው አብዛኛው ልምምድ በሀገራቸው የዓየር ክልል ላይ ይደረጋል፡፡
በፈረንጆቹ ሰኔ 12 እና ሰኔ 24 መካከል ባሉት ቀናት በአንዱ የሚጀመረው ልምምድ ሩሲያን የምታዋስነዋን የስቶኒያ የዓየር ክልል እና ዩክሬንን የምታዋስነውን የሮማኒያ የዓየር ክልል ማካተቱን አር ቲ ዘግቧል፡፡
በቅርቡ (ኔቶን) የተቀላቀለችውን ፊንላንድ ጨምሮ በአጠቃላይ 24 ሀገራት በልምምዱ ላይ ይሳተፋሉም ተብሏል።
ቡድኑን ገና ያልተቀላቀለችው ስዊድንም ትካፈልበታለች፡፡